Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 110:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤ “አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታ የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፥ በጠላቶችህም መካከል ግዛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር ኀያል ገዢነትህን ከጽዮን አንሥቶ ያሰፋዋል፤ እንዲህም ይልሃል፦ “በጠላቶችህ ላይ ንገሥ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 110:2
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዙ​ሪ​ያው ያላ​ችሁ ሁሉ ስሙ​ንም የም​ታ​ውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠን​ካ​ራ​ውም ሽመል፥ እን​ዴት ተሰ​በረ! ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሱ​ለት።


ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር አላ​ፍ​ር​ምና፤ አስ​ቀ​ድሞ አይ​ሁ​ዳ​ዊን፥ ደግ​ሞም አረ​ማ​ዊን፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትን ሁሉ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሉ ነውና።


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።


ወደ መቅ​ደ​ሱም መዝ​ጊያ መለ​ሰኝ፤ እነ​ሆም ውኃ ከቤቱ መድ​ረክ በታች ወደ ምሥ​ራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከት ነበ​ርና፤ ውኃ​ውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመ​ሠ​ዊ​ያው በደ​ቡብ በኩል ይወ​ርድ ነበር።


ከተ​መ​ረ​ጡት ጫፎ​ች​ዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬ​ዋ​ንም በላች፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም በትር ይሆን ዘንድ የበ​ረታ በትር የለ​ባ​ትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለል​ቅ​ሶም ይሆ​ናል።


ሕግ ከጽ​ዮን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይወ​ጣ​ልና ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ መጥ​ተው፥ “ኑ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ፥ ወደ ያዕ​ቆብ አም​ላክ ቤት እን​ውጣ፤ እር​ሱም መን​ገ​ዱን ያስ​ተ​ም​ረ​ናል፤ በጎ​ዳ​ና​ውም እን​ሄ​ዳ​ለን” ይላሉ።


ዐስ​በው ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ። በአ​ር​ያ​ምም ዐመ​ፃን ተና​ገሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ይዘህ በወ​ን​ዞ​ቹና በመ​ስ​ኖ​ዎቹ፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ዎ​ቹም ላይ እጅ​ህን ዘርጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ች​ንም አውጣ’ ” በለው።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ውሰድ፤ በግ​ብፅ ውኆች፥ በወ​ን​ዞ​ቻ​ቸው፥ በመ​ስ​ኖ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በኩ​ሬ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ እጅ​ህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆ​ናል፤” በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በዕ​ን​ጨት ዕቃና በድ​ን​ጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች