የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በላሙ ላይ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከወይፈኑ ጋራ በግማሽ ሂን ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ የላመ ዱቄት ቍርባን ዐብራችሁ አምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከወይፈኑ ጋር የኢን መስፈሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን ታቀርባለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከወይፈኑ ጋር ሦስት ኪሎ በግማሽ ሊትር ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርብ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከወይፈኑ ጋር የኢን መስፈሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታቀርባለህ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 15:9
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኦር​ናም ዳዊ​ትን፥ “ለአ​ንተ ውሰ​ደው፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ፤ እነሆ፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ቹን፥ ለእ​ን​ጨ​ትም የአ​ው​ድ​ማ​ውን ዕቃ፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን ስን​ዴ​ውን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፥ ሁሉን እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።


ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት፥ ስለ ኅብ​ስተ ገጽም፥ ዘወ​ት​ርም በሰ​ን​በ​ትና በመ​ባቻ ስለ ማቅ​ረብ ስለ እህሉ ቍር​ባ​ንና ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ ስለ በዓ​ላ​ትም፥ ስለ ተቀ​ደ​ሱ​ትም ነገ​ሮች፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስለ​ሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አን​ጻር በሰ​ሜ​ንና በደ​ቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነ​ርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ካህ​ናቱ ከሁሉ ይልቅ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ምግብ የሚ​በ​ሉ​ባ​ቸው ቤቶች ናቸው። ስፍ​ራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር፥ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት ያኖ​ራሉ።


በበ​ዓ​ላ​ትና በክ​ብረ በዓል ቀኖች የእ​ህሉ ቍር​ባን ለወ​ይ​ፈኑ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እን​ደ​ሚ​ች​ለው ያህል፥ ለአ​ንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ይሆ​ናል።


እን​ዲሁ ዘወ​ትር ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ጠቦ​ቱ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ዘይ​ቱ​ንም በየ​ማ​ለ​ዳው ያቀ​ር​ባሉ።”


የእ​ህ​ሉም ቍር​ባን ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ይሁን፤ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባን እጁ እንደ ቻለ ያህል ይሁን፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ያቅ​ርብ።


ለወ​ይ​ፈ​ኑም አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እንደ ቻለው ያህል፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህሉ ቍር​ባን ያቅ​ርብ።


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተወ​ግ​ዶ​አል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ውያ የም​ታ​ገ​ለ​ግሉ ካህ​ናቱ፥ አል​ቅሱ።


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


“በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ዓመት የሞ​ላ​ቸ​ውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ት​ንም አን​ዲት የዓ​መት እን​ስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህ​ልም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ይወ​ስ​ዳል።


“የአ​ሮን ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ለፊት የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የመ​ሥ​ዋ​ዕት ሥር​ዐት ይህ ነው።


የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህል ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ትና የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት፥ የቅ​ድ​ስ​ናና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ለተ​ደ​ረገ ቍር​ባን፥ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ ወይን ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ለሌላ መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ስእ​ለ​ትን ለመ​ፈ​ጸም፥ ወይም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከላም ወገን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ዘ​ጋጅ፥


ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወይ​ፈን ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ው​ራው በግ ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥


የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


በወሩ መባቻ ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን እንደ ሕጋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።


እር​ስ​ዋም ከእ​ርሱ ጋር አንድ የሦ​ስት ዓመት ወይ​ፈን፥ እን​ጀራ፥ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴ​ሎም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች። ልጃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።