Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 28:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋራ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን ግማሽ የወይን ጠጅ፣ ከአውራው በግ ጋራ የሂን አንድ ሦስተኛ፣ ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋራ የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ ይቅረብ፤ ይህም በየወሩ መባቻ ዓመቱን ሙሉ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የመጠጥ ቁርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ተገቢ ለሆነው የመጠጥ መባ ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሁለት ሊትር መጠጥ፥ ከአውራው በግ ጋር አንድ ተኩል ሊትር መጠጥ፥ ከእያንዳንዱም ጠቦት ጋር አንድ ሊትር የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ በዓመቱ ሙሉ፥ ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ስለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት የተሰጠው የሥርዓት መመሪያ ይኸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 28:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጠቦት ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።


ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም የኢን መስ​ፈ​ሪያ የሆነ መል​ካም ዱቄት አራ​ተኛ እጅ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ወይም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድ​ርግ።


በላሙ ላይ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።


የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ለአ​ንድ ጠቦት የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተ​ኛው እጅ ነው፤ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መጠጥ ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ።


ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ችው መጠን እንደ ሕጉ፥


ከዚ​ያም በኋላ ዘወ​ትር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የመ​ባ​ቻ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት፥ ሰውም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የሰ​ጠ​ውን ቍር​ባን አቀ​ረቡ።


መል​ካ​ሙን የስ​ንዴ ዱቄት ብታ​መጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣ​ና​ችሁ በእኔ ዘንድ አስ​ጸ​ያፊ ነው፤ መባ​ቻ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ሰን​በ​ቶ​ቻ​ች​ሁን፥ ታላ​ቋን፥ ቀና​ች​ሁን፥ ጾማ​ች​ሁ​ንና ሥራ መፍ​ታ​ታ​ች​ሁን አል​ወ​ድም።


ሞአ​ብ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ላይ የሚ​ሠ​ዋ​ውን፥ ለአ​ማ​ል​ክ​ቱም የሚ​ያ​ጥ​ነ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አለ​ቃ​ውም በሰ​ን​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ስድ​ስት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት አንድ አውራ በግ ይሁን፤


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት ቀር​ቶ​አ​ልና እና​ንተ ካህ​ናት! ማቅ ታጥ​ቃ​ችሁ አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የመ​ሠ​ውያ አገ​ል​ጋ​ዮች! ዋይ በሉ፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች