Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ዘኍል 15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የመ​ሥ​ዋ​ዕት ሕግ

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

2 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥

3 በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ቢሆን በበ​ዓ​ላ​ች​ሁም ቢሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእ​ለ​ቱን አብ​ዝ​ታ​ችሁ በአ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።

4 ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ርብ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ የሆነ የመ​ል​ካም ዱቄት መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል።

5 ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም የኢን መስ​ፈ​ሪያ የሆነ መል​ካም ዱቄት አራ​ተኛ እጅ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ወይም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድ​ርግ።

6 ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።

7 ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሦስ​ተኛ እጅ ወይን ታቀ​ር​ባ​ለህ።

8 ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ለሌላ መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ስእ​ለ​ትን ለመ​ፈ​ጸም፥ ወይም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከላም ወገን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ዘ​ጋጅ፥

9 በላሙ ላይ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።

10 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ለተ​ደ​ረገ ቍር​ባን፥ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ ወይን ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።

11 “እን​ዲሁ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ወይ​ፈን፥ ወይም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አውራ በግ፥ ወይም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ተባት የበግ ወይም የፍ​የል ጠቦት ይደ​ረ​ጋል።

12 እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጃ​ች​ሁት ቍጥር፥ እን​ዲሁ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።

13 የሀ​ገር ልጅ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን ባቀ​ረበ ጊዜ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።

14 መጻ​ተ​ኛም ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ፥ ወይም በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን በእ​ሳት ቢያ​ቀ​ርብ እና​ንተ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን እርሱ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።

15 ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።

16 ለእ​ና​ን​ተና ከእ​ና​ንተ ጋር ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ አንድ ሕግና አንድ ፍርድ ይሆ​ናል።”

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ፤ ተና​ገ​ረው፦

18 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤

19 ወደ​ማ​መ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ንተ የም​ድ​ሪ​ቱን እን​ጀራ በበ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ቍር​ባን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።

20 መጀ​መ​ሪያ ከም​ታ​ደ​ር​ጉት ሊጥ አንድ እን​ጎቻ ለይ​ታ​ችሁ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከአ​ው​ድ​ማ​ውም እን​ደ​ም​ት​ለ​ዩት ቍር​ባን እን​ዲሁ ትለ​ያ​ላ​ችሁ።

21 መጀ​መ​ሪ​ያም ከም​ታ​ደ​ር​ጉት ሊጥ የተ​ለየ ቍር​ባን እስከ ልጅ ልጃ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


ስላ​ል​ታ​ወ​ቀው ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት

22 “ብት​በ​ድ​ሉም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ትእ​ዛ​ዛት ሁሉ ባታ​ደ​ርጉ፥

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካዘ​ዘ​በት ከፊ​ተ​ኛው ቀን ጀምሮ ወደ ፊትም እስከ ልጅ ልጃ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እንደ አዘ​ዛ​ችሁ ባታ​ደ​ርጉ፥

24 በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት ያል​ታ​ወቀ ኀጢ​አት ቢኖር፥ ማኅ​በሩ ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ንጹሕ ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባሉ። የእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና የመ​ጠጡ ቍር​ባ​ንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀ​ር​ባሉ።

25 ካህ​ኑም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ባለ​ማ​ወቅ ነበ​ርና ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውና ስላ​ለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባሉ።

26 በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ዘንድ ያለ ዕው​ቀት ተደ​ር​ጎ​አ​ልና ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ወደ እና​ን​ተም ለሚ​መጣ መጻ​ተኛ ስር​የት ይደ​ረ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።

27 “አንድ ሰው ሳያ​ውቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢ​አት አን​ዲት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ፍየል ያቀ​ር​ባል።

28 ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

29 ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።

30 የሀ​ገር ልጅ ቢሆ​ንም ወይም መጻ​ተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰድ​ቦ​አል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል።

31 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ናቀ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀጢ​አቱ በራሱ ላይ ነው።”


ሰን​በ​ትን ስለ ሻረ የተ​ቀ​ጣው ሰው

32 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ድረ በዳ ነበሩ፤ አንድ ሰውም በሰ​ን​በት ቀን ዕን​ጨት ሲለ​ቅም አገኙ።

33 በሰ​ን​በት ቀን ዕን​ጨት ሲለ​ቅም ያገ​ኙ​ትም ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ አመ​ጡት።

34 እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አል​ፈ​ረ​ዱ​ምና በግ​ዞት ቤት አዋ​ሉት።

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ሰው​ዬው ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት” አለው።

36 ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት።


በል​ብስ ላይ ስለ​ሚ​ደ​ረግ ዘፈር

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

38 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እነ​ር​ሱም በት​ው​ል​ዳ​ቸው ሁሉ በል​ብ​ሳ​ቸው ጫፍ ዘርፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ በዘ​ር​ፉም ሁሉ ላይ ሰማ​ያዊ ፈትል ያደ​ርጉ ዘንድ እዘ​ዛ​ቸው።

39 እር​ሱም በዘ​ርፉ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ትመ​ለ​ከ​ቱ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትእ​ዛ​ዛት ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ታደ​ር​ጉ​አ​ቸ​ው​ማ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱን በመ​ከ​ተል ያመ​ነ​ዘ​ራ​ች​ሁ​ባ​ትን የሕ​ሊ​ና​ች​ሁ​ንና የዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ፈቃድ አት​ከ​ተሉ።

40 ትእ​ዛ​ዙን ታስ​ቡና ታደ​ርጉ ዘንድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ቅዱ​ሳን ትሆኑ ዘንድ፤

41 እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ችሁ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።”

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች