ማቴዎስ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ የተባለው ልብድዮስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፥ ቶማስና ቀራጩ ማቴዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊልጶስ፥ በርቶሎሜዎስ፥ ቶማስ፥ ቀራጩ ማቴዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ታዴዎስ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥ |
ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፤
ፈሪሳዊውም ቆመና እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማኞችና እንደ ዐመፀኞች፥ እንደ አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ያላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ።
ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይኖቹንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያነሣ አልወደደም፤ ደረቱንም እየመታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢኣተኛውን ይቅር በለኝ’ አለ።
ጌታችን ኢየሱስም ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይህ ነው” አለ።
የአስቆሮቱ ሰው ያይደለ ይሁዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ያይደለ ለእኛ ራስህን ትገልጥ ዘንድ እንዳለህ የተናገርኸው ምንድን ነው?” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብሬአችሁ ስኖር አታወቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እንግዲህ እንዴት አብን አሳየን ትላለህ?
ስምዖን ጴጥሮስ፥ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ፥ ከገሊላ ቃና የሆነው ናትናኤል፥ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎችም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት አብረው ነበሩ።
ወደ ማደሪያቸውም በደረሱ ጊዜ ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴዎስ፥ በርተሎሜዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖን፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ።
እርሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ አመለከታቸው፤ ከወኅኒ ቤትም እግዚአብሔር እንደ አወጣው ነገራቸው፤ “ይህንም ለያዕቆብና ለወንድሞች ሁሉ ንገሩ” አላቸው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
የሰጠኝንም ጸጋ ዐውቀው አዕማድ የሚሏቸው ያዕቆብና ኬፋ፥ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ፥ እነርሱም ወደ አይሁድ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን።