Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ቀነናዊው ስምዖን፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ በርተሎሜውስ፥ ማቴዎስ፥ ቶማስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ታዴዎስ፥ ቀነናዊው ስምዖን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ በርቶሎሜዎስ፥ ማቴዎስ፥ ቶማስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ታዴዎስ፥ ተቀናቃኙ ስምዖን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 3:18
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በደ​ረሱ ጊዜ ጴጥ​ሮስ፥ ዮሐ​ንስ፥ ያዕ​ቆብ፥ እን​ድ​ር​ያስ፥ ፊል​ጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴ​ዎስ፥ በር​ተ​ሎ​ሜ​ዎስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆብ፥ ቀና​ተ​ኛው ስም​ዖን፥ የያ​ዕ​ቆብ ልጅ ይሁ​ዳም ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በት ሰገ​ነት ወጡ።


ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና “ተከተለኝ፤” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤


የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


ነገር ግን የጌ​ታ​ችን ወን​ድም ያዕ​ቆ​ብን እንጂ ከሐ​ዋ​ር​ያት ሌላ አላ​የ​ሁም።


ከዚ​ህም በኋላ ለያ​ዕ​ቆብ ታየው፤ ኋላም ለሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ፤


እንደ ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ሁሉና፥ እንደ ጌታ​ችን ወን​ድ​ሞች እንደ ኬፋም ከሴ​ቶች እኅ​ታ​ች​ንን ይዘን ልን​ዞር አይ​ገ​ባ​ን​ምን?


በማ​ግ​ሥ​ቱም ጳው​ሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕ​ቆብ ገባ፤ ቀሳ​ው​ስ​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ።


እነ​ር​ሱም ጸጥ ባሉ ጊዜ ያዕ​ቆብ መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙኝ።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማስ፥ ከገ​ሊላ ቃና የሆ​ነው ናት​ና​ኤል፥ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆ​ችና ሌሎ​ችም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለት አብ​ረው ነበሩ።


የአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው ያይ​ደለ ይሁ​ዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓ​ለም ያይ​ደለ ለእኛ ራስ​ህን ትገ​ልጥ ዘንድ እን​ዳ​ለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ምን​ድን ነው?” አለው።


ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማ​ስም፥ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ደቀ መዛ​ሙ​ርት፥ “እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ሞት ዘንድ እን​ሂድ” አላ​ቸው።


እር​ሱም “መጥ​ታ​ችሁ እዩ” አላ​ቸው፤ ሄደ​ውም የሚ​ኖ​ር​በ​ትን አዩ፤ ያን ዕለ​ትም እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ በእ​ርሱ ዘንድ ዋሉ።


ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።


ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ፥ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?


የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፤ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤


አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች