Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማ​ስም፥ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ደቀ መዛ​ሙ​ርት፥ “እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ሞት ዘንድ እን​ሂድ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ለተቀሩት ደቀ መዛሙርት፣ “እኛም ሄደን ከርሱ ጋራ እንሙት” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዲዲሞስ የሚሉትም ቶማስ ለሌሎቹ ደቀ መዛሙርት “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም እንሂድ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በዚህ ጊዜ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ሌሎቹን ደቀ መዛሙርት፥ “ከእርሱ ጋር እንድንሞት እኛም እንሂድ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርቱ፦ “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:16
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥


ጴጥሮስም “ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን፥ ከቶ አልክድህም፤” አለው። ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ደግሞ እንደዚሁ አሉ።


እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥


እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እኔ ለመ​ታ​ሰ​ርም ቢሆን፥ ለሞ​ትም ቢሆን እንኳ ከአ​ንተ ጋራ ለመ​ሄድ የተ​ዘ​ጋ​ጀሁ ነኝ” አለው።


ማቴ​ዎ​ስና ቶማስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆ​ብና ቀናዒ የሚ​ባ​ለው ስም​ዖን።


ታም​ኑም ዘንድ እኔ በዚያ ባለ​መ​ኖሬ ስለ እና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ ነገር ግን ኑ፥ ወደ እርሱ እን​ሂድ።”


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ አይ​ሁድ ሊወ​ግ​ሩህ ይሹ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ዛሬ ደግሞ አንተ ወደ​ዚያ ልት​ሄድ ትሻ​ለ​ህን?” አሉት።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን አሁን ልከ​ተ​ልህ አል​ች​ልም? እኔ ነፍ​ሴ​ንም እንኳ ቢሆን ስለ አንተ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።


ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን የማ​ና​ውቅ እን​ግ​ዲህ መን​ገ​ዱን እን​ዴት እና​ው​ቃ​ለን?” አለው።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማስ፥ ከገ​ሊላ ቃና የሆ​ነው ናት​ና​ኤል፥ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆ​ችና ሌሎ​ችም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለት አብ​ረው ነበሩ።


ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በደ​ረሱ ጊዜ ጴጥ​ሮስ፥ ዮሐ​ንስ፥ ያዕ​ቆብ፥ እን​ድ​ር​ያስ፥ ፊል​ጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴ​ዎስ፥ በር​ተ​ሎ​ሜ​ዎስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆብ፥ ቀና​ተ​ኛው ስም​ዖን፥ የያ​ዕ​ቆብ ልጅ ይሁ​ዳም ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በት ሰገ​ነት ወጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች