Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሐዋርያት ሥራ 15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ ቢጽ ሐሳ​ው​ያን

1 ከይ​ሁዳ ሀገ​ርም የወ​ረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካል​ተ​ገ​ዘ​ራ​ችሁ ልት​ድኑ አት​ች​ሉም” እያሉ ወን​ድ​ሞ​ችን ያስ​ተ​ምሩ ነበር።

2 ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።

3 ከቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም በተ​ላኩ ጊዜ ወደ ሰማ​ር​ያና ወደ ፊንቄ ደር​ሰው አሕ​ዛብ ወደ ሃይ​ማ​ኖት እንደ ተመ​ለሱ ነገ​ሩ​ቸ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰ​ኙ​አ​ቸው።

4 ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው።

5 ነገር ግን ካመ​ኑት ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን አን​ዳ​ን​ዶች ተነ​ሥ​ተው፥ “ትገ​ዝ​ሩ​አ​ቸው ዘን​ድና የሙ​ሴን ሕግ እን​ዲ​ጠ​ብቁ ታዝ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ይገ​ባል” አሉ።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ የሐ​ዋ​ር​ያት ጉባኤ

6 ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስ​ትም ስለ​ዚህ ነገር የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ያዩ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።

7 ብዙ ክር​ክ​ርም ከተ​ከ​ራ​ከሩ በኋላ ጴጥ​ሮስ ተነ​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአ​ሕ​ዛብ ከአፌ የወ​ን​ጌ​ሉን ቃል እን​ዳ​ሰ​ማ​ቸ​ውና እን​ዲ​ያ​ምኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ እንደ መረ​ጠኝ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

8 ልብን የሚ​ያ​ውቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእኛ እንደ ሰጠን መን​ፈስ ቅዱ​ስን በመ​ስ​ጠት መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው።

9 ልባ​ቸ​ው​ንም በእ​ም​ነት አን​ጽቶ ከእኛ አል​ለ​ያ​ቸ​ውም።

10 አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ኑት፤ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ልን​ሸ​ከ​መው ያል​ቻ​ል​ነ​ውን ቀን​በር በደቀ መዛ​ሙ​ርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭ​ና​ላ​ችሁ?

11 ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ እን​ድን ዘንድ እን​ታ​መ​ና​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ ይድ​ናሉ።”

12 ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲና​ገሩ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን አዳ​መ​ጡ​አ​ቸው።


ስለ ያዕ​ቆብ ንግ​ግር

13 እነ​ር​ሱም ጸጥ ባሉ ጊዜ ያዕ​ቆብ መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙኝ።

14 ስም​ዖ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ አሕ​ዛ​ብን ይቅር እን​ዳ​ላ​ቸ​ውና ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ለስሙ ሕዝ​ብን እንደ መረጠ ተና​ግ​ሮ​አል።

15 በዚ​ህም መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ እንደ ተና​ገረ የነ​ቢ​ያት ቃል ይስ​ማ​ማል።

16 ከዚ​ህም በኋላ የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት መልሼ እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤ ፍራ​ሽ​ዋ​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤

17 የቀ​ሩት ሰዎ​ችና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤

18 ከጥ​ንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የታ​ወቀ ነው።

19 “አሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለሱ አሕ​ዛብ ላይ ሥር​ዐት አታ​ክ​ብዱ እላ​ች​ኋ​ለሁ።

20 ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።

21 ሙሴም ከጥ​ንት ጀምሮ በየ​ከ​ተ​ማዉ የሚ​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ነበር፤ በየ​ም​ኵ​ራ​ቡም በየ​ሰ​ን​በቱ ያነ​ብ​ቡት ነበር።”


ስለ ሐዋ​ር​ያት ጉባኤ መል​እ​ክት

22 ከዚ​ህም በኋላ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሕዝ​ቡም ሁሉ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ አን​ጾ​ኪያ የሚ​ል​ኳ​ቸ​ውን ሰዎች ይመ​ርጡ ዘንድ ተስ​ማሙ፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልም የተ​ማ​ሩ​ትን ሰዎች በር​ና​ባስ የተ​ባለ ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን መረጡ።

23 እን​ዲህ የም​ትል መል​እ​ክ​ትም በእ​ጃ​ቸው ጻፉ፤ “ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትና ከቀ​ሳ​ው​ስት ከወ​ን​ድ​ሞ​ችም በአ​ን​ጾ​ኪያ፥ በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅያ ለሚ​ኖሩ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ትድ​ረስ፤ ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።

24 ያላ​ዘ​ዝ​ና​ቸው ሰዎች ከእኛ ወጥ​ተው፦ ‘ትገ​ዘሩ ዘን​ድና የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ትጠ​ብቁ ዘንድ ይገ​ባ​ች​ኋል’ ብለው በነ​ገር እንደ አወ​ኩ​አ​ች​ሁና ልባ​ች​ሁን እንደ አና​ወ​ጡት ሰም​ተ​ናል።

25 ሁላ​ችን ከተ​ሰ​በ​ሰ​ብን በኋላ በአ​ንድ ቃል በየን፤ አንድ ሆነ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ እና​ንተ የም​ን​ል​ካ​ቸ​ውን ሰዎች መረ​ጥን።

26 እነ​ር​ሱም ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አሳ​ል​ፈው የሰጡ ሰዎች ናቸው።

27 ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን ልከ​ና​ቸ​ዋ​ልና እነ​ርሱ በቃ​ላ​ቸው ይህን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።

28 ሥር​ዐት እን​ዳ​ና​ከ​ብድ ሌላም ሸክም እን​ዳ​ን​ጨ​ምር መን​ፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እና​ዝ​ዛ​ች​ኋ​ለን።

29 ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”

30 እነ​ር​ሱም ተል​ከው ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስ​በው የተ​ላ​ከ​ውን ደብ​ዳቤ ሰጡ​አ​ቸው።

31 እነ​ር​ሱም አን​ብ​በው እጅግ ደስ አላ​ቸው፥ ተጽ​ና​ኑም።

32 ይሁ​ዳና ሲላ​ስም መም​ህ​ራን ነበ​ሩና አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም በብዙ ቃል አጽ​ና​ኑ​አ​ቸው።

33 በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተ​ቀ​መጡ በኋላ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ተሰ​ና​ብ​ተው በሰ​ላም ወደ ሐዋ​ር​ያት ተመ​ለሱ።

34 ሲላስ ግን በዚያ ሊቈይ ወደደ።

35 ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም በአ​ን​ጾ​ኪያ ቈዩ፤ ከሌ​ሎች ብዙ ሰዎች ጋርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፤ አስ​ተ​ማ​ሩም።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባስ እንደ ተለ​ያዩ

36 ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ጳው​ሎስ በር​ና​ባ​ስን፦“እን​ግ​ዲ​ህስ እን​መ​ለ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባስ​ተ​ማ​ር​ን​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ያሉ​ትን ወን​ድ​ሞች እን​ጐ​ብ​ኛ​ቸው፤ እን​ዴት እን​ዳ​ሉም እን​ወቅ” አለው።

37 በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ።

38 ጳው​ሎስ ግን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሊወ​ስ​ደው አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እነ​ርሱ በጵ​ን​ፍ​ልያ ሳሉ ትቶ​አ​ቸው ሄዶ​አ​ልና፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ለሥራ አል​መ​ጣም ነበ​ርና።

39 ስለ​ዚ​ህም ተኰ​ራ​ር​ፈው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ፤ በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆ​ስን ይዞ በመ​ር​ከብ ወደ ቆጵ​ሮስ ሄደ።

40 ጳው​ሎስ ግን ሲላ​ስን መረጠ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ከሰ​ጡት በኋላ ሄደ።

41 በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅ​ያም እየ​ዞረ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን አጽ​ናና።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች