Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 18:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱን ባይሰማ ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማ፣ እንደ አሕዛብና እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ ቍጠረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቁጠረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱንም አልሰማም ቢል ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም የማይሰማ ከሆነ እንደ አረመኔና ተጸጽቶ እንደማይመለስ ኃጢአተኛ ቊጠረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 18:17
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከም​ር​ኮም ተመ​ል​ሰው የመ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን ከም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ለይ​ተው ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው የነ​በ​ሩት ሁሉ ፋሲ​ካ​ውን በሉ፤


በት​እ​ዛዜ አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩት እንደ አሕ​ዛብ ሕግ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።”


ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥


የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


“አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።


ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ሊሰ​ሙት ወደ እርሱ ይቀ​ርቡ ነበር።


ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ከዘ​ማ​ው​ያን ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ በዚህ መል​እ​ክት ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


እን​ግ​ዲህ በሚ​ነ​ቅፉ ሰዎች ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከሩ አት​ድ​ፈሩ፤ ከጓ​ደ​ኛው ጋር በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ሊከ​ራ​ከር የሚ​ችል አለን? በደ​ጋ​ጎች ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን? ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር ክር​ክር ያለው ቢኖ​ርም በቅ​ዱ​ሳን ዘንድ ይከ​ራ​ከር፤ በሚ​ነ​ቅ​ፉና በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ግን አይ​ደ​ለም።


ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች