ሉቃስ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እላችኋለሁ፦ ባለቀባችሁ ጊዜ እነርሱ በዘለዓለም ቤታቸው ይቀበሉአችሁ ዘንድ በዐመፃ ገንዘብ ለእናንተ ወዳጆች አድርጉበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የዚህ ዓለም ገንዘብ ባለቀ ጊዜ በዘላለም ቤት ተቀባይነት እንዲኖራችሁ፣ በዚሁ ገንዘብ ወዳጆችን ለራሳችሁ አፍሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እላችኋለሁ፤ የዐመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘለዓለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ አማካኝነት ወዳጆችን ለራሳችሁ አብጁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ በዐመፅ ገንዘብ ወዳጆች አብጁ እላችኋለሁ፤ ይህን ብታደርጉ ገንዘባችሁ አልቆባችሁ ባዶ እጃችሁን ስትቀሩ ወዳጆቻችሁ ለዘለዓለም በሚኖሩበት ቤት ይቀበሉአችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። |
“መንፈስ ከእኔ ይወጣልና፥ የሁሉንም ነፍስ ፈጥሬአለሁና ለዘለዓለም አልቀስፋችሁም፤ ሁልጊዜም አልቈጣችሁም።
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
ሀብታችሁን ሸጣችሁ ምጽዋት ስጡ፤ ሌባ በማያገኝበት ነቀዝም በማያበላሽበት፥ የማያረጅ ከረጢት፥ የማያልቅም መዝገብ በሰማያት ለእናንተ አድርጉ።
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚችል አገልጋይ የለም፤ ካልሆነም አንዱን ይወድዳል፤ ሁለተኛውንም ይጠላል፤ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል፤ ለሁለተኛውም እንቢ ይላል፤ እንዲሁም እናንተ ገንዘብ እየወደዳችሁ ለእግዚአብሔር መገዛት አትችሉም።”
ወደእርሱም ተመልክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምንድን ነው?” አለ፤ መልአኩም እንዲህ አለው፥ “ጸሎትህም ምጽዋትህም መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጎአል።