Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሉቃስ 14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሆዱ የተ​ነ​ፋ​ውን ሰው እንደ ፈወሰ

1 ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።

2 እነ​ሆም፥ ሆዱ የተ​ነፋ አንድ ሰው በፊቱ ነበር።

3 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ ሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ች​ንና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ “በሰ​ን​በት ድውይ መፈ​ወስ ይገ​ባ​ልን? ወይስ አይ​ገ​ባም?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው።

4 እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ይዞም ፈወ​ሰ​ውና ሰደ​ደው።

5 “ከእ​ና​ንተ በሬው ወይም አህ​ያው በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ የወ​ደ​ቀ​በት አንድ ሰው ቢኖር ዕለ​ቱን በሰ​ን​በት ቀን ያነ​ሣው የለ​ምን?” አላ​ቸው።

6 ስለ​ዚ​ህም ነገር ሊመ​ል​ሱ​ለት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።


በራ​ስጌ መቀ​መ​ጥን ስለ​ሚ​ወዱ ሰዎች

7 በምሳ ላይ ለነ​በ​ሩ​ትም ወደ ላይ​ኛው ወን​በር ሲሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ባያ​ቸው ጊዜ ምሳሌ መስሎ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።

8 እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለምሳ የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ በላ​ይ​ኛው መቀ​መጫ አት​ቀ​መጥ፤ ምና​ል​ባት ከአ​ንተ የሚ​በ​ልጥ ይመጣ ይሆ​ናል።

9 በኋላ ያ አን​ተ​ንም እር​ሱ​ንም የጠራ መጥቶ፦ ይህን ቦታ ለእ​ርሱ ተው​ለት ይል​ሃ​ልና፤ ያን​ጊ​ዜም አፍ​ረህ ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ወደ ዝቅ​ተኛ ቦታም ትወ​ር​ዳ​ለህ።

10 የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ ግን የጠ​ራህ በመጣ ጊዜ ወዳጄ ወደ ላይ​ኛው መቀ​መጫ ውጣ ይልህ ዘንድ በታ​ች​ኛው መቀ​መጫ ተቀ​መጥ፤ ያን​ጊ​ዜም ከአ​ንተ ጋር ለማ​ዕድ በተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ፊት ክብር ይሆ​ን​ል​ሃል።

11 ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”

12 የጠ​ራ​ው​ንም እን​ዲህ አለው፥ “በበ​ዓል ምሳ ወይም ራት በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፥ ዘመ​ዶ​ች​ህ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ህን፥ ባለ​ጸ​ጎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ጥራ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሩ​ሃ​ልና፤ ብድ​ርም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና።

13 ነገር ግን በበ​ዓል ምሳ በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ችን፥ እጅና እግ​ርም የሌ​ላ​ቸ​ውን ጥራ።

14 አን​ተም ብፁዕ ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ከ​ፍ​ሉህ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን ጻድ​ቃን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ዋጋ​ህን ታገ​ኛ​ለህ።”

15 ለምሳ ከተ​ቀ​መ​ጡ​ትም አንዱ ይህን ሰምቶ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እህል የሚ​በላ ብፁዕ ነው” አለው።


ለምሳ ስለ መጠ​ራት

16 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አንድ ሰው ታላቅ ምሳ አደ​ረ​ገና ብዙ ሰዎ​ችን ጠራ።

17 ለምሳ የተ​ጠ​ሩ​በ​ትም ቀን በደ​ረሰ ጊዜ የታ​ደ​ሙ​ትን ይጠ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱም ሄዶ የታ​ደ​ሙ​ትን፦ አሁን ምሳ​ውን ፈጽ​መን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ና​ልና ኑ አላ​ቸው።

18 ሁሉም በአ​ንድ ቃል ተባ​ብ​ረው እንቢ አሉ፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፦ እርሻ ገዝ​ች​አ​ለሁ፤ ሄጄም ላያት እሻ​ለሁ፤ እንቢ እንደ አላ​ልሁ ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው።

19 ሁለ​ተ​ኛ​ውም፦ አም​ስት ጥማድ በሬ ገዝ​ቻ​ለሁ፤ ላያ​ቸ​ውና ልፈ​ት​ና​ቸው እሄ​ዳ​ለሁ፤ እንደ መጣሁ፥ እንቢ እንደ አላ​ል​ሁም ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው።

20 ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው።

21 አገ​ል​ጋ​ዩም ተመ​ልሶ ለጌ​ታው ይህ​ንኑ ነገ​ረው፤ ያን​ጊ​ዜም ባለ​ቤቱ ተቈጣ፤ አገ​ል​ጋ​ዩ​ንም፦ ፈጥ​ነህ ወደ አደ​ባ​ባ​ይና ወደ ከተ​ማው ጐዳና ሂድ፤ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጣ​ልኝ አለው።

22 ከዚ​ህም በኋላ አገ​ል​ጋዩ፦ አቤቱ እንደ አዘ​ዝ​ኸኝ አደ​ረ​ግሁ፤ ገናም ቦታ አለ አለው።

23 ጌታ​ውም አገ​ል​ጋ​ዩን፦ ወደ መን​ገ​ዶ​ችና ወደ ከተ​ማው ቅጥር ፈጥ​ነህ ሂድና ቤቴ እን​ዲ​መላ ይገቡ ዘንድ ግድ በላ​ቸው አለው።

24 ከእ​ነ​ዚህ ከታ​ደ​ሙት ሰዎች አንዱ ስን​ኳን ማዕ​ዴን እን​ደ​ማ​ይ​ቀ​ም​ሳት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።”


ጌታን ስለ መከ​ተል

25 ከዚ​ህም በኋላ ብዙ ሰዎች አብ​ረ​ውት ሲሄዱ መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው።

26 “ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።

27 መስ​ቀ​ሉን ተሸ​ክሞ ሊከ​ተ​ለኝ የማ​ይ​መጣ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።”


ቤት ስለ​ሚ​ሠ​ራው ሰው ምሳሌ

28 “ከእ​ና​ን​ተም ወገን የግ​ንብ ቤት መሥ​ራት የሚ​ወድ ቢኖር ይጨ​ር​ሰው ዘንድ የሚ​ችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ የሚ​ፈ​ጅ​በ​ትን የማ​ያ​ስብ ማን ነው?

29 መሠ​ረ​ቱን ጥሎ መጨ​ረስ ያቃ​ተ​ውም እንደ ሆነ ያዩት ሁሉ፥

30 ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀመረ፤ ግን መጨ​ረስ ተሳ​ነው’ እያሉ ሊዘ​ብ​ቱ​በት ይጀ​ም​ራሉ።

31 ንጉ​ሥም ሌላ​ውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ሊሄድ ቢወድ ሁለት እልፍ ይዞ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ውን በአ​ንድ እልፍ ሊዋ​ጋው ይችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ ይመ​ክር የለ​ምን?

32 ያለ​ዚያ ግን፥ ገና በሩቁ ሳለ አማ​ላ​ጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ ዕርቅ ይለ​ም​ናል።

33 እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ዚሁ ከእ​ና​ንተ ወገን ከሁሉ ያል​ወጣ፥ የእ​ርሱ ገን​ዘብ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያል​ተ​ለየ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።

34 “ጨው መል​ካም ነው፤ ጨው አልጫ ከሆነ እን​ግ​ዲህ በምን ያጣ​ፍ​ጡ​ታል?

35 ለም​ድ​ርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆ​ለ​ያም ቢሆን አይ​ረ​ባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች