Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እን​ግ​ዲህ ጌታዬ ከም​ግ​ብ​ናዬ የሻ​ረኝ እንደ ሆነ በቤ​ታ​ቸው ይቀ​በ​ሉኝ ዘንድ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እኔ ዐው​ቃ​ለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከመጋቢነት የተሻርሁ እንደ ሆነ፣ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን ዐውቃለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ፤’ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ቈይ! የማደርገውን ዐውቃለሁ፤ ከመጋቢነት ሥራዬ ስሰናበት፥ በቤታቸው የሚቀበሉኝ ወዳጆች እንዲኖሩኝ አደርጋለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 16:4
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።


ያም መጋቢ ዐስቦ እን​ዲህ አለ፦ ‘ምን ላድ​ርግ? አሁን ጌታዬ ከመ​ጋ​ቢ​ነቴ ይሽ​ረ​ኛል፤ ማረስ አል​ች​ልም፤ ለመ​ለ​መ​ንም አፍ​ራ​ለሁ።


ለጌ​ታ​ውም ዕዳ የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትን ጠራ​ቸው፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም፦ ‘ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት ነው’ አለው።


እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ባለ​ቀ​ባ​ችሁ ጊዜ እነ​ርሱ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ይቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ዘንድ በዐ​መፃ ገን​ዘብ ለእ​ና​ንተ ወዳ​ጆች አድ​ር​ጉ​በት።


ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፤ የሥጋም ነው፤ የአጋንንትም ነው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች