Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጌታ​ውም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ከብ​ር​ሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓ​ለ​ማ​ቸው ይራ​ቀ​ቃ​ሉና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ጌታውም አጭበርባሪውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ከመሰሎቻቸው ጋራ በሚኖራቸው ግንኙነት ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 16:8
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና፤ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም።


ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።


“በጥ​ቂት የሚ​ታ​መን በብዙ ይታ​መ​ናል፤ በጥ​ቂት የሚ​ያ​ም​ፅም በብ​ዙም ቢሆን ያም​ፃል።


የብ​ር​ሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ በብ​ር​ሃን እመኑ” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ ሄደ፤ ተሰ​ወ​ራ​ቸ​ውም።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።


እን​ግ​ዲህ ጌታዬ ከም​ግ​ብ​ናዬ የሻ​ረኝ እንደ ሆነ በቤ​ታ​ቸው ይቀ​በ​ሉኝ ዘንድ የማ​ደ​ር​ገ​ውን እኔ ዐው​ቃ​ለሁ።’


ኑ፤ እን​ጠ​በ​ብ​ባ​ቸው፤ የበዙ እን​ደ​ሆነ ጦር​ነት በመ​ጣ​ብን ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ላይ ተደ​ር​በው በኋ​ላ​ችን ይወ​ጉ​ና​ልና፥ ከም​ድ​ራ​ች​ንም ያስ​ወ​ጡ​ና​ልና።”


እባ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ከፈ​ጠ​ራ​ቸው ከም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይልቅ ተን​ኰ​ለኛ ነበር። እባ​ብም ሴቲ​ቱን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ አት​ብሉ ያላ​ችሁ ለም​ን​ድን ነው?” አላት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገ​ባሉ፥ ይጋ​ባ​ሉም፤ ይወ​ል​ዳሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም።


ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።


ለአ​ም​ኖ​ንም የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ የሚ​ባል ወዳጅ ነበ​ረው፤ ኢዮ​ና​ዳ​ብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።


ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዐመ​ፀ​ኛው ዳኛ ያለ​ውን ስሙ።


ጴጥሮስም “ከእንግዶች” ባለው ጊዜ ኢየሱስ “እንኪያስ ልጆቻቸው ነጻ ናቸው።


አሁ​ንም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ሁሉ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀር፤ ለበ​ዓል ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ውም ሁሉ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም” አላ​ቸው። ኢዩ ግን የበ​ዓ​ልን አገ​ል​ጋ​ዮች ያጠፋ ዘንድ በተ​ን​ኮል ይህን አደ​ረገ።


በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።


ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፦ ‘አን​ተሳ ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብ​ዳ​ቤህ፤ ተቀ​ም​ጠህ ሰማ​ንያ አለ​ብኝ ብለህ ፈጥ​ነህ ጻፍ’ አለው።


ያን ዓለ​ምና የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ሊወ​ርሱ የሚ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚያ ግን አያ​ገ​ቡም፤ አይ​ጋ​ቡም።


የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች