የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በውኑ ስለ​ዚህ ነገር በመ​ቅ​ሠ​ፍት አል​ጐ​በ​ኝ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታዲያ ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንደዚህ ዐይነቱንስ ሕዝብ፣ አልበቀልምን?”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀስፋቸውምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ በዚህ ሁሉ ነገር እነርሱን ልቀጣቸውና እንደነዚህ ያሉትንስ ሕዝብ ልበቀላቸው አይገባኝምን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 9:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ወዮ​ላ​ቸው! በጠ​ላ​ቶች ላይ ቍጣዬ አይ​በ​ር​ድም፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


በሸ​ለቆ ውስጥ ያሉ የለ​ዘቡ ድን​ጋ​ዮች ዕድል ፋን​ታሽ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእ​ነ​ር​ሱም የመ​ጠጥ ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ሻል፤ የእ​ህ​ል​ንም ቍር​ባን አቅ​ር​በ​ሻል። እን​ግ​ዲህ በዚህ ነገር አል​ቈ​ጣ​ምን?


እር​ስ​ዋም ለፍ​ጹም ጥፋት ሆና​ለች፤ ስለ እኔም ምድር ሁሉ ባድማ ሆና​ለች፤ በል​ቡም የሚ​ያ​ኖ​ራት የለም።


በሚ​ኖ​ሩ​ባት ሰዎች ክፋት ምድ​ሪቱ የም​ታ​ለ​ቅ​ሰ​ውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚ​ደ​ር​ቀው እስከ መቼ ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጻ​ሜ​ያ​ች​ንን አያ​ይም ብለ​ዋ​ልና እን​ስ​ሶ​ችና ወፎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋል።


ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ ሸሽ​ተው ነበር።


በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?


በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?


ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ።


አቤቱ! እሳት የም​ድረ በዳ​ውን ውበት አጥ​ፍ​ቶ​አ​ልና፥ ነበ​ል​ባ​ሉም የዱ​ሩን ዛፍ ሁሉ አቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ወደ​ቀች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሣም፤ በም​ድ​ርዋ ላይ ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ትም የለም።