የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 26:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በፊ​ታ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባት​ሰ​ሙኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ባትሰሙኝና የሰጠኋችሁን ሕጌን ባትጠብቁ፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም በላቸው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ለመሄድ እኔን ባትሰሙ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ተናገር አለኝ፦ “እኔ እግዚአብሔር የሰጠኋችሁን ሕግ ባትከተሉና ባትታዘዙኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም በላቸው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባትሰሙኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 26:4
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ እኔን ትታ​ችሁ ወደ ኋላ ብት​መ​ለሱ ለሙሴ በፊ​ታ​ችሁ የሰ​ጠ​ሁ​ትን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ባት​ጠ​ብቁ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥


እንቢ ብት​ሉና ባት​ሰ​ሙኝ ግን ሰይፍ ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ነገር ግን የሰ​ን​በ​ትን ቀን እን​ድ​ት​ቀ​ድሱ፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክ​ምን ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች እን​ዳ​ት​ገቡ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ባት​ሰ​ሙኝ፥ በበ​ሮ​ችዋ ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ግን​ቦች ትበ​ላ​ለች፤ አት​ጠ​ፋ​ምም።


ነገር ግን ይህን ቃል ባት​ሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እን​ዲ​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


እስከ ዛሬም ድረስ አላ​ረ​ፉም፤ አል​ፈ​ሩ​ምም፤ በእ​ና​ን​ተና በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ባኖ​ር​ሁት ሕጌና ሥር​ዐቴ አል​ሄ​ዱም።


ስላ​ጠ​ና​ች​ሁት ዕጣን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ስለ በደ​ላ​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ስላ​ል​ሰ​ማ​ችሁ፥ በሕ​ጉና በሥ​ር​ዐ​ቱም፥ በም​ስ​ክ​ሩም ስላ​ል​ሄ​ዳ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግ​ኝ​ታ​ች​ኋ​ለች።”


ስለ​ዚህ በሴሎ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እን​ዲሁ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት፥ እና​ን​ተም በም​ት​ተ​ማ​መ​ኑ​በት ቤት ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋ​ችሁ ስፍራ እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እኔም ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ የማ​ኖ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ካገ​ባ​ኋ​ቸው በኋላ፥ ከበ​ሉም፥ ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ይስ​ታሉ፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ወደ ማም​ለክ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እኔ​ንም ያስ​ቈ​ጡ​ኛል፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ።


ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ያኖ​ራት ሕግ ይህች ናት፤


ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ማ​ኖ​ራት እን​ደ​ዚ​ህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆ​ነች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።