Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ዘዳግም 11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


መታ​ዘዝ የሚ​ያ​ስ​ገ​ኘው ጥቅም

1 “አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደድ፤ ሕጉ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም፥ ፍር​ዱ​ንም በዘ​መ​ንህ ሁሉ ጠብቅ።

2 ዛሬ ልጆ​ቻ​ችሁ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተግ​ሣጽ፥ ታላ​ቅ​ነ​ቱ​ንም፥ የጸ​ና​ችም እጁን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክን​ዱን፥ ያዩና ያወቁ እን​ዳ​ይ​ደሉ ዕወቁ።

3 በግ​ብ​ፅም መካ​ከል በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖ​ንና በሀ​ገሩ ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጋ​ትን ተአ​ም​ራ​ቱ​ንና ድንቅ ሥራ​ዉን፥

4 በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም ጊዜ በኤ​ር​ትራ ባሕር ውኃ እን​ዳ​ሰ​ጠ​ማ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ቸው፥ በግ​ብፅ ጭፍራ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን፥

5 ወደ​ዚህ ስፍራ እስ​ክ​ት​መጡ ድረስ በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁን ሁሉ፥

6 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መካ​ከል ምድር አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ በዋ​ጠ​ቻ​ቸው በሮ​ቤል ልጅ በኤ​ል​ያብ ልጆች በዳ​ታ​ንና በአ​ቤ​ሮን ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፤

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ጋ​ቸ​ውን ታላ​ላቅ ሥራ​ዎች ሁሉ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋ​ልና።


የተ​ስ​ፋ​ይቱ ምድር በረ​ከት

8 “በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበ​ዙም ዘንድ፥ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን የም​ት​ሻ​ገ​ሩ​ላ​ትን ምድር እን​ድ​ት​ወ​ር​ሷት ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ር​ሱና ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ላይ ዕድ​ሜ​ያ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም።

10 ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር፥ በአ​ት​ክ​ልት ስፍራ እን​ደ​ሚ​ዘሩ ዘር​ህን እንደ ዘራ​ህ​ባት፥ በእ​ግ​ር​ህም እን​ዳ​ጠ​ጣ​ሃት፥ እንደ ወጣ​ህ​ባት እንደ ግብፅ ምድር አይ​ደ​ለ​ችም።

11 ነገር ግን ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ የም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ተራ​ሮ​ችና ሜዳ​ዎች ያሉ​ባት ሀገር ናት፤ በሰ​ማይ ዝናብ ውኃ ትረ​ካ​ለች።

12 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጐ​በ​ኛት ሀገር ናት፤ ከዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ እስከ ዓመቱ መጨ​ረሻ ድረስ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእ​ር​ስዋ ላይ ነው።

13 “እና​ንተ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዜን ፈጽ​ማ​ችሁ ብት​ሰሙ፥

14 እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ትሰ​በ​ስብ ዘንድ በየ​ጊ​ዜው የበ​ል​ጉን ዝና​ብና የክ​ረ​ም​ቱን ዝናብ ለም​ድ​ርህ ይሰ​ጣል።

15 በሜ​ዳህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ችህ ሣርን ይሰ​ጣል፤ ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ።

16 ልባ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ስት፥ ፈቀቅ እን​ዳ​ትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት እን​ዳ​ታ​መ​ልኩ፥ እን​ዳ​ት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ተጠ​ን​ቀቁ።

17 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ባ​ችሁ፥ ዝና​ብም እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ፥ ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን እን​ዳ​ት​ሰጥ ሰማ​ይን እን​ዳ​ይ​ዘ​ጋ​ባ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ዳ​ት​ጠፉ ተጠ​ን​ቀቁ።

18 “እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን ቃሎች በል​ባ​ች​ሁና በነ​ፍ​ሳ​ችሁ አኑሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለም​ል​ክት በእ​ጃ​ችሁ ላይ እሰ​ሩ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁኑ።

19 ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ በቤ​ትም ሲቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም ሲሄዱ፥ ሲተ​ኙም፥ ሲነ​ሡም እን​ዲ​ነ​ጋ​ገ​ሩ​በት፤

20 በቤ​ትህ መቃ​ኖ​ችና በደ​ጃ​ፍ​ህም በሮች ላይ ጻፈው።

21 በም​ድር ላይ የሰ​ማ​ይን ዘመን ያህል ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ዘመ​ና​ችሁ የል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ዘመን ይረ​ዝም ዘንድ፤

22 አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያወ​ጣል፤ ከእ​ና​ን​ተም የሚ​በ​ል​ጡ​ትን፥ የሚ​በ​ረ​ቱ​ት​ንም አሕ​ዛብ ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።

24 የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።

25 በእ​ና​ን​ተም ፊት ማንም መቆም አይ​ች​ልም፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ማስ​ፈ​ራ​ታ​ች​ሁን፥ ማስ​ደ​ን​ገ​ጣ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ረ​ግ​ጡ​አት ምድር ሁሉ ላይ ያኖ​ራል።

26 “እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን አኖ​ራ​ለሁ፤

27 በረ​ከ​ትም፥ እኔ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰሙ ነው፤

28 መር​ገ​ምም፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ባት​ሰሙ፥ ዛሬ ካዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የማ​ታ​ው​ቁ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ፥ ብታ​መ​ል​ኳ​ቸ​ውም ነው።

29 አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ አን​ተን ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​ባት ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፥ በረ​ከ​ቱን በገ​ሪ​ዛን ተራራ፥ መር​ገ​ሙ​ንም በጌ​ባል ተራራ ታኖ​ራ​ለህ።

30 እነ​ር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፥ ከፀ​ሐይ መግ​ቢያ ካለ​ችው መን​ገድ በኋላ በዓ​ረባ በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ በጌ​ል​ጌላ ፊት ለፊት በረ​ዥሙ ዛፍ አጠ​ገብ ናቸው።

31 አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ጣ​ችሁ ለሁ​ል​ጊዜ የሚ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር ትገ​ቡና ትወ​ርሱ ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ትቀ​መ​ጡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁም።

32 እኔም ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ የማ​ኖ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች