Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ባ​ችሁ፥ ዝና​ብም እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ፥ ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን እን​ዳ​ት​ሰጥ ሰማ​ይን እን​ዳ​ይ​ዘ​ጋ​ባ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ዳ​ት​ጠፉ ተጠ​ን​ቀቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚያም የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችሁ ይነድዳል፤ እርሱም ዝናብ እንዳይዘንብ፣ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይቈጣል፤ ሰማያትን ዘግቶ ምድሪቱን ዝናብ እንዳይዘንብባትና ፍሬ እንዳትሰጥ ያደርጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር ከሚሰጣችሁ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የእግዚአብሔርም ቁጣ እንዳይነድድባችሁ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 11:17
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


“አን​ተን ስለ በደሉ ሰማይ ቢዘጋ፥ ዝና​ብም ባይ​ዘ​ንብ፥ በዚ​ህም ስፍራ ቢጸ​ልዩ፥ ለስ​ም​ህም ቢና​ዘዙ፥ ባስ​ጨ​ነ​ቅ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥


“አን​ተን ስለ በደሉ ሰማ​ያት በተ​ዘጉ ጊዜ፥ ዝና​ብም ባል​ዘ​ነበ ጊዜ፥ በዚህ ስፍራ ቢጸ​ልዩ፥ ስም​ህ​ንም ቢያ​ከ​ብሩ፥ ባዋ​ረ​ድ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥


ዝናብ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ሰማ​ያ​ቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን እን​ጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አን​በ​ጣን ባዝ​ዘው፥ ወይም በሕ​ዝቤ ላይ ቸነ​ፈር ብሰ​ድድ፥


እነሆ፥ ዝና​ብን ከሰ​ማይ ቢከ​ለ​ክል ምድ​ርን ያደ​ር​ቃ​ታል፤ እን​ደ​ገና ቢተ​ዋ​ትም ትጠ​ፋ​ለች፤ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለ​ችም።


የት​ዕ​ቢ​ታ​ች​ሁን ስድብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሰማ​ያ​ች​ሁ​ንም እንደ ብረት፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም እንደ ናስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ጕል​በ​ታ​ች​ሁም በከ​ንቱ ያል​ቃል፤ ምድ​ራ​ች​ሁም እህ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥም፤ የዱር ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም።


መከር ሳይ​ደ​ርስ ገና ከሦ​ስት ወር በፊት ዝና​ብን ከለ​ከ​ል​ኋ​ችሁ፤ በአ​ን​ድም ከተማ ላይ አዘ​ነ​ብሁ፤ በሌ​ላ​ውም ከተማ ላይ እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ አደ​ረ​ግሁ፤ በአ​ንድ ወገን ዘነበ፤ ያል​ዘ​ነ​በ​በ​ትም ወገን ደረቀ።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ካገ​ባ​ኋ​ቸው በኋላ፥ ከበ​ሉም፥ ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ይስ​ታሉ፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ወደ ማም​ለክ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እኔ​ንም ያስ​ቈ​ጡ​ኛል፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ።


ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ከም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ድ​ት​ጠፉ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በእ​ና​ንተ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ፈጽ​ሞም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።


በመ​ካ​ከ​ልህ ያለው አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ አም​ላክ ነውና የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቁጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ብህ፥ ከም​ድ​ርም ፊት እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ ከተ​ቈ​ጣ​ባ​ችሁ ከቍ​ጣ​ውና ከመ​ዓቱ የተ​ነሣ ፈራሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች