Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 11:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፣ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከርሱም ጋራ ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “አምላካችሁን ጌታን ትወዱ ዘንድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ስለዚህም እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውደዱ፤ በእርሱ መንገድም በመጓዝ ለእርሱ ታማኞች ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 11:22
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።


አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል፤ በስ​ሙም ማል።


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደድ፤ ሕጉ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም፥ ፍር​ዱ​ንም በዘ​መ​ንህ ሁሉ ጠብቅ።


“እና​ንተ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዜን ፈጽ​ማ​ችሁ ብት​ሰሙ፥


አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ ሁል​ጊ​ዜም በመ​ን​ገዱ ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ብት​ሰማ፥ በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስት ከተ​ሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትጨ​ም​ራ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ሪቱ ትቀ​መጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይ​ወ​ትህ፥ የዘ​መ​ን​ህም ርዝ​መት ነውና አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥ​ና​ውም።”


ለአ​ንተ ያዘ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ፥ ምስ​ክ​ሩ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም አጥ​ብ​ቀህ ጠብቅ።


ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች