Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን ቃሎች በል​ባ​ች​ሁና በነ​ፍ​ሳ​ችሁ አኑሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለም​ል​ክት በእ​ጃ​ችሁ ላይ እሰ​ሩ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እነዚህን ቃሎቼን፣ በልባችሁና በአእምሯችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግንባራችሁም ላይ ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “እነዚህን ቃሎቼን፥ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፥ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር በልቡናችሁና በአእምሮአችሁ ቅረጹአቸው፤ መታሰቢያም ይሆኑላችሁ ዘንድ እነርሱን በክንዳችሁ ላይ እሰሩ፤ በግንባራችሁም ላይ እንደማስታወሻ አኑሩአቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 11:18
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በብ​ርቱ እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት ፥ ከዐ​ይ​ኖ​ች​ህም እን​ደ​ማ​ይ​ርቅ ነገር ይሁ​ን​ልህ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ረ​ታች እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በአ​ፍህ ይሆን ዘንድ በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት፥ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እንደ መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ን​ልህ።


ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።


ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤


ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ሩኝ ሌላ መን​ገ​ድና ሌላ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፤


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ዝ​ዙ​በት ዛሬ የም​መ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ሁን ቃል ሁሉ በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት።


በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።


ስለ​ዚ​ህም ከሰ​ማ​ነው ነገር ምን​አ​ል​ባት እን​ዳ​ን​ወ​ሰድ ለእ​ርሱ አብ​ዝ​ተን ልን​ጠ​ነ​ቀቅ ይገ​ባ​ናል።


ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ፥ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች