የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ብዙ ጊዜ ቈየ፤ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ፣ የሳኦል ቤት ግን እየተዳከመ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ዐይነት በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቈየ፤ ሆኖም ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳኦል ቤተሰብ እየተዳከመ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ብዙ ዘመን ጦርነት ሆነ፥ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 3:1
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”


በዚ​ያም ቀን እጅግ ጽኑ ሰልፍ ሆነ፤ በዳ​ዊ​ትም ሰዎች ፊት አበ​ኔ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ተሸ​ነፉ።


ኢዮ​አ​ብም ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተመ​ለሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ እስ​ራ​ኤ​ልን አላ​ሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውም፤ ደግ​መ​ውም አል​ተ​ዋ​ጉም።


ከአ​ሕ​ዛብ ጠብ አድ​ነኝ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፤ የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝብ ተገ​ዛ​ልኝ።


በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ጦር​ነት ሆኖ ሳለ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ያበ​ረታ ነበር።


ዳዊ​ትም እየ​በ​ረታ፥ ከፍ እያ​ለም ሄደ፤ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።


በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሮ​ብ​ዓ​ምና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከል ጦር​ነት ነበረ።


አሳና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ሲዋጉ ኖሩ።


በአ​ሳና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በባ​ኦስ መካ​ከል በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ጦር​ነት ነበረ።


ዳዊ​ትም ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና እየ​በ​ረታ ሄደ።


በኬ​ብ​ሮን ለዳ​ዊት የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። በኵሩ አም​ኖን ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዶለ​ህያ ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቢ​ግያ፥


ነገር ግን ወደ መን​ገዴ እንደ ምመ​ለስ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ፤ እጆ​ችም የነጹ ናቸ​ውና፤ ደስ​ታ​ዬን አገ​ኛ​ታ​ለሁ።


ጅማ​ሬ​ህም ታናሽ ቢሆ​ንም እንኳ ፍጻ​ሜህ ቍጥር አይ​ኖ​ረ​ውም።


የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤ የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን አሳ​የን፥ አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ስጠን።


ሥጋ መን​ፈስ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ መን​ፈ​ስም ሥጋ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ የም​ት​ሹ​ት​ንም እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እርስ በር​ሳ​ቸው ይጣ​ላሉ።


ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና።


አየሁም፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድልም እየነሣ ወጣ፤ ድል ለመንሣት።