Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 84 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፦ ምድ​ር​ህን ይቅር አልኽ። የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ምርኮ መለ​ስህ።

2 የሕ​ዝ​ብ​ህን ኀጢ​አት ይቅር አልህ፤ ዐበ​ሳ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሰወ​ርህ።

3 መዓ​ት​ህ​ንም ሁሉ አስ​ወ​ገ​ድህ፤ ከቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለ​ስህ።

4 አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ሆይ፥ መል​ሰን፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኛ መልስ።

5 ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ቈ​ጣን፥ ቍጣ​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አታ​ስ​ረ​ዝም።

6 አንተ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተመ​ለ​ስ​ልን፥ አድ​ነ​ንም፤ ሕዝ​ብ​ህም በአ​ንተ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

7 አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን አሳ​የን፥ አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ስጠን።

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን አደ​ም​ጣ​ለሁ፤ ሰላ​ምን ለሕ​ዝ​ቡና ለጻ​ድ​ቃኑ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ እርሱ ለሚ​መ​ልሱ ይና​ገ​ራ​ልና።

9 ነገር ግን ክብር በም​ድ​ራ​ችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚ​ፈ​ሩት ቅርብ ነው።

10 ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።

11 ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱን ይሰ​ጣል፥ ምድ​ርም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች።

13 ጽድቅ በፊቱ ይሄ​ዳል፥ ፍለ​ጋ​ው​ንም በመ​ን​ገድ ውስጥ ይተ​ዋል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች