በዚያም ሦስቱ የሦርህያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ፥ አሣሄልም ነበሩ፤ የአሣሄልም እግሮቹ ፈጣኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳቋም ሯጭ ነበረ።
2 ሳሙኤል 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሣሄልም የአበኔርን ፍለጋ ተከታተለ፤ አበኔርንም ከማሳደድ ቀኝና ግራ አላለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሣሄልም ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሳይል አበኔርን ተከታተለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤኔርን ለመያዝ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሳይል ተከተለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔርን አባሮ ለመያዝ በቀጥታ ወደ እርሱ ሮጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሣሄልም የአበኔርን ፍለጋ ተከታተለ፥ አበኔርንም ከማሳደድ ቀኝና ግራ አላለም። |
በዚያም ሦስቱ የሦርህያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ፥ አሣሄልም ነበሩ፤ የአሣሄልም እግሮቹ ፈጣኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳቋም ሯጭ ነበረ።
አበኔርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብላቴኖቹም አንድ ጐልማሳ ያዝ፤ መሣሪያውንም ለራስህ ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ይገድሉት ዘንድ ይጠባበቁ ነበር።
ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ። እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥ የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው። እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥ አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።
አገልጋዬ ሙሴ እንደ አዘዘህ ሕግን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ ጽና፤ እጅግም በርታ፤ ሁሉን እንዴት እንደምትሠራ ታውቅ ዘንድ ከእርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አትበል።