Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

2 ነገሥት 22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመነ መን​ግ​ሥት
( 2ዜ.መ. 34፥1-2 )

1 ኢዮ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የስ​ም​ንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ከባ​ሱ​ሮት የሆነ የአ​ዳያ ልጅ ይዲያ ነበ​ረች።

2 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።

3 በን​ጉ​ሡም በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ንጉሡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጸሓፊ የሜ​ሱ​ላ​ምን ልጅ የኤ​ሴ​ል​ዩን ልጅ ሳፋ​ንን እን​ዲህ ሲል ላከው፦

4 “ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬል​ቅዩ ወጥ​ተህ ደጃ​ፉን የሚ​ጠ​ብቁ ከሕ​ዝቡ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የገ​ባ​ውን ወርቅ ቍጠር።

5 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ላሉት ሠራ​ተ​ኞች አለ​ቆች ይስ​ጡት፤ እነ​ር​ሱም የተ​ና​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ጠ​ግ​ኑት ሠራ​ተ​ኞች፥

6 ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችና ለጠ​ራ​ቢ​ዎች፥ ለድ​ን​ጋ​ይም ወቃ​ሪ​ዎች፥ መቅ​ደ​ሱ​ንም ለመ​ጠ​ገን እን​ጨ​ት​ንና የተ​ወ​ቀ​ረ​ውን ድን​ጋይ ለሚ​ገዙ ይክ​ፈ​ሉት።”

7 ነገር ግን እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ይሠሩ ነበ​ርና የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ገን​ዘብ አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር።


የሕጉ መጽ​ሐፍ መገ​ኘት

8 ታላቁ ካህ​ንም ኬል​ቅ​ያስ ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቻ​ለሁ” አለው፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው፥ እር​ሱም አነ​በ​በው።

9 ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለን​ጉ​ሡም፥ “በመ​ቅ​ደሱ የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ አፈ​ሰ​ሱት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ሥራ ለመ​ሥ​ራት ለተ​መ​ደ​ቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገ​ረው።

10 ጸሓ​ፊው ሳፋ​ንም ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕግ መጽ​ሐፍ ሰጥ​ቶ​ኛል” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።

11 ንጉ​ሡም የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።

12 ንጉ​ሡም ካህ​ኑን ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ዩ​ንም ልጅ ዓክ​ቦ​ርን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዓስ​ያን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦

13 “አባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ር​ስዋ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚ​ህ​ችን መጽ​ሐፍ ቃል ስላ​ል​ሰሙ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁ​ዳም ሁሉ ስለ​ዚ​ችም ስለ​ተ​ገ​ኘ​ችው መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ።

14 እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኬል​ቅ​ያ​ስና አኪ​ቃም ዓክ​ቦ​ርም ሳፋ​ንና ዓሳ​ያም ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢ​ዪቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በዚያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ነገ​ሩ​አት።

15 እር​ስ​ዋም አለ​ቻ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ለላ​ካ​ችሁ ሰው እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዳ​ነ​በ​በው እን​ደ​ዚህ መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ።

17 በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ለላ​ካ​ችሁ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ግን እን​ዲህ በሉት፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ሰማ​ኸው ቃል፥

19 ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

20 ነገሩ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም።” ይህ​ንም ለን​ጉሡ ነገ​ሩት።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች