የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጌ​ታ​ህ​ንም ቤት ሰጠ​ሁህ፤ የጌ​ታ​ህ​ንም ሚስ​ቶች በብ​ብ​ትህ ጣል​ሁ​ልህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ቤት ሰጠ​ሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበ​ለጠ እጨ​ም​ር​ልህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፣ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ አስታቀፍሁህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ኖሮ፣ ከዚህ በላይ ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በእቅፍህ አኖርኩ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤትም ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ኖሮ፤ ከዚህ በላይ ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መንግሥቱንና ሚስቶቹን ሰጠሁህ፤ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ አነገሥኩህ፤ ይህም ሁሉ እንኳ የማይበቃህ ቢሆን ኖሮ በተጨማሪ እጥፍ አድርጌ በሰጠሁህ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፥ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 12:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል።


ባለ​ጠ​ጋ​ውም እጅግ ብዙ የበ​ግና የላም መንጋ ነበ​ረው።


የይ​ሁ​ዳም ሰዎች መጥ​ተው በይ​ሁዳ ቤት ይነ​ግሥ ዘንድ ዳዊ​ትን በዚያ ቀቡት። ሳኦ​ልን የቀ​በ​ሩት የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሰዎች ናቸው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።


በኬ​ብ​ሮን በይ​ሁዳ ላይ ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉና በይ​ሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።


ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እኔ በፊ​ትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪ​ያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።


ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ለእ​ናቱ መልሶ፥ “ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳን ለአ​ዶ​ን​ያስ ለምን ትለ​ም​ኚ​ለ​ታ​ለሽ? ታላቅ ወን​ድሜ ነውና መን​ግ​ሥ​ትን ደግሞ ለም​ኚ​ለት፤ ካህ​ኑም አብ​ያ​ታ​ርና የሶ​ር​ህያ ልጅ የጭ​ፍ​ሮች አለቃ ኢዮ​አብ ደግሞ ከእ​ርሱ ጋር ናቸው” አላት።


ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።


ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?


ለም​ርኮ ሳስ​ተህ ለምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህም? ለም​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረ​ግህ?”