Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋራ ይተኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከቤተሰብህ አንዱ ተነሥቶ ችግር እንዲያደርስብህ የማደርግ መሆኔን በመሐላ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው በምሰጥበት ጊዜ ይህ ነገር እንደሚፈጸም ትገነዘባለህ፤ እርሱም ከሚስቶችህ ጋር በቀን ብርሃን ይገናኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፥ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 12:11
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ አቤ​ሴ​ሎም በኬ​ብ​ሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበ​ኞ​ችን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ላከ።


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እን​ሽሽ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ የም​ን​ድ​ን​በት የለ​ን​ምና፤ ፈጥኖ እን​ዳ​ይ​ዘን፥ ክፉም እን​ዳ​ያ​መ​ጣ​ብን፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ልፍ ስለት እን​ዳ​ይ​መታ ፈጥ​ና​ችሁ እን​ሂድ” አላ​ቸው።


በን​ጉሡ ዘንድ ሊፋ​ረዱ ለሚ​መጡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ልብ ማረከ።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወ​ገቤ የወ​ጣው ልጄ ነፍ​ሴን ይሻል፤ ይል​ቁ​ንስ ይህ የኢ​ያ​ሚን ልጅ እን​ዴት ነዋ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​ታ​ልና ተዉት፥ ይር​ገ​መኝ።


ሚስቴ ሌላ​ውን ሰው ደስ ታሰኝ። ልጆ​ቼም ይዋ​ረዱ።


ነቢ​ዩም ቢታ​ለል፥ ቃል​ንም ቢና​ገር፥ ያን ነቢይ ያታ​ለ​ልሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እጄ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ልቡም እን​ዳ​ይ​ስት ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ርሱ አያ​ብዛ፤ ወር​ቅና ብርም ለእ​ርሱ እጅግ አያ​ብዛ።


ሚስት ታገ​ባ​ለህ፤ ሌላም ሰው ይነ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ቤት ትሠ​ራ​ለህ፤ በእ​ር​ሱም አት​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም፤ ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ከእ​ር​ሱም አት​ለ​ቅ​ምም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች