Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለም​ርኮ ሳስ​ተህ ለምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህም? ለም​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረ​ግህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ታዲያ እግዚአብሔርን ለምን አልታዘዝህም? ለምርኮውስ ተስገብግበህ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ለምን አደረግህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ታዲያ የጌታን ቃል ለምን አልታዘዝህም? ለምርኮውስ ተስገብግበህ በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ለምን አደረግህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ታዲያ ስለምን ትእዛዙን አልፈጸምክም? ለምርኮስ በመሳሳትና በመስገብገብ እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ነገር ስለምን አደረግህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 15:19
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ።


ይህ ስሜ የተ​ጠ​ራ​በት ቤት በዐ​ይ​ና​ችሁ የሌ​ቦች ዋሻ ነውን? እነሆ፥ እኔ አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።


በአ​ም​ላ​ኩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ከነ​ቢዩ ከኤ​ር​ም​ያስ ፊት፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የተ​ነሣ አላ​ፈ​ረም።


በሄ​ኖ​ምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ። መተ​ተ​ኛም ነበረ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ ያስ​ቈ​ጣ​ውም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ወ​ጣ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ያለ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።


ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ሰ​ማሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ከኝ መን​ገድ ሄጃ​ለሁ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግ​ንም አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም ፈጽሜ አጥ​ፍ​ቻ​ለሁ።


ሙሴም አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? ይህ ለእ​ና​ንተ መል​ካም አይ​ደ​ለም።


አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች