የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ለሁ” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሠ​ዊ​ያን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር፣ “ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ” ባለበት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠዊያዎችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔር እንዲመለክበት ባዘዘው ስፍራ ማለትም በቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን አቆመ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲመለክበት ባዘዘው ስፍራ ማለትም በቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን አቆመ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም “ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ፤” ባለው በእግዚአብሔር ቤት መሠዊያዎችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 21:4
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ዙፋ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


ባሪ​ያህ ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ሌሊ​ትና ቀን የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።


የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ያሠ​ሩ​ትን በአ​ካዝ ቤት ሰገ​ነት ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች፥ ምና​ሴም ያሠ​ራ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሁ​ለቱ ወለ​ሎች ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ንጉሡ አስ​ፈ​ረ​ሳ​ቸው፤ ከዚ​ያም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፥ ትቢ​ያ​ቸ​ው​ንም በቄ​ድ​ሮን ፈፋ ጣለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ራ​ቅ​ሁት ይሁ​ዳን ከፊቴ አር​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ትን ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና፦ ስሜ በዚያ ይሆ​ናል ያል​ሁ​ት​ንም ቤት እጥ​ላ​ለሁ” አለ።


እርሱ፦ ሕዝ​ቤን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠ​ራ​በት ዘንድ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም። በሕ​ዝቤ እስ​ራ​ኤል ላይም ይነ​ግሥ ዘንድ ሰውን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።


ከፊቴ አስ​ወ​ግ​ዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠ​ሩ​አት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቁ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ ውስጥ ናትና፤


ያረ​ክ​ሱ​ትም ዘንድ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን አኖሩ።


ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”


የይ​ሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉ ነገ​ርን ሠር​ተ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ያረ​ክ​ሱ​ትም ዘንድ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት ቤት ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን አኑ​ረ​ዋል።


ይህን ደግሞ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ኛል፤ በዚያ ቀን መቅ​ደ​ሴን አር​ክ​ሰ​ዋል፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ሽረ​ዋል።


ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው በሠዉ ጊዜ ፥ በዚ​ያው ቀን ያረ​ክ​ሱት ዘንድ ወደ መቅ​ደሴ ገቡ፤ እነ​ሆም በቤቴ ውስጥ እን​ደ​ዚህ አደ​ረጉ።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።