ዘዳግም 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከከተሞቻችሁ ሁሉ በአንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደዚያም ትመጣላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዳሩ ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆነው፣ በነገዶቻችሁ መካከል የሚመርጠውን ስፍራ እሹ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ነገር ግን ጌታ አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆነው፥ በነገዶቻችሁ መካከል የሚመርጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደ እዚያም ስፍራ ትሄዳላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ ስሙን በዚያ ያኖር ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ ትመጣላችሁ፥ ማደሪያውንም ትሻላችሁ። ምዕራፉን ተመልከት |