የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልጆ​ቹም በመ​ን​ገዱ አል​ሄ​ዱም፤ ነገር ግን ረብ ለማ​ግ​ኘት ፈቀቅ አሉ፤ መማ​ለጃ በሉ፤ ፍርድ አደሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ልጆቹ የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጕቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልጆቹ ግን የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጉቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን የአባታቸውን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የገንዘብ ጥቅም ፈላጊዎች ሆነው ጉቦ እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልጆቹም በመንገዱ አልሄዱም፥ ነገር ግን ረብ ለማግኘት ፈቀቅ አሉ፥ ጉቦም እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 8:3
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “ነገ​ርና ክር​ክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈ​ር​ድ​ለት ዘንድ በሀ​ገር ላይ ፈራጅ አድ​ርጎ ማን በሾ​መኝ?” ይል ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።


አባ​ቴና እናቴ ጥለ​ው​ኛ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ተቀ​በ​ለኝ።


አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው።


“በፍ​ርድ የድ​ሀ​ውን ፍርድ አታ​ጣ​ምም።


መማ​ለ​ጃን አት​ቀ​በል፤ መማ​ለጃ የዐ​ይ​ና​ማ​ዎ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ እው​ነ​ተኛ ቃል​ንም ያጣ​ም​ማ​ልና።


ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።


በጽ​ድቅ የሚ​ሄድ፥ ቅን ነገ​ር​ንም የሚ​ና​ገር፥ በደ​ል​ንና ኀጢ​አ​ትን የሚ​ጠላ፥ መማ​ለ​ጃን ከመ​ጨ​በጥ እጁን የሚ​ያ​ራ​ግፍ፥ ደም ማፍ​ሰ​ስን ከመ​ስ​ማት ጆሮ​ቹን የሚ​ደ​ፍን፥ ክፋ​ት​ንም ከማ​የት ዐይ​ኖ​ቹን የሚ​ጨ​ፍን ነው።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


አሁ​ንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳል፤ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም አር​ፋ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ልጆቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊ​ታ​ችሁ ሄድሁ።


የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።