Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሳይ​ቀባ፥ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ራ​ል​ኛል፥ ያድ​ነ​ኛ​ልም፤ ምን ያስ​ፈ​ራ​ኛል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ይ​ወቴ መታ​መ​ኛዋ ነው፤ ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛል?

2 ክፉ​ዎች ሥጋ​ዬን ይበሉ ዘንድ በቀ​ረቡ ጊዜ፥ የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩኝ እነ​ዚያ ጠላ​ቶቼ ደከሙ፥ ወደ​ቁም።

3 ሠራ​ዊ​ትም ቢጠ​ላኝ ልቤ አይ​ፈ​ራ​ብ​ኝም፤ ሠራ​ዊ​ትም ቢከ​ቡኝ በእ​ርሱ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ።

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ዲት ነገር ለመ​ን​ሁት፥ እር​ስ​ዋ​ንም እሻ​ለሁ፤ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅ​ደ​ሱም አገ​ለ​ግል ዘንድ።

5 በመ​ከ​ራዬ ቀን በድ​ን​ኳኑ ሸሽ​ጎ​ኛ​ልና፥ በድ​ን​ኳ​ኑም መሸ​ሸ​ጊያ ሰው​ሮ​ኛ​ልና፥ በዓ​ለ​ትም ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጎ​ኛ​ልና።

6 እነሆ፥ አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ዞርሁ በድ​ን​ኳ​ኑም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋሁ፥ እል​ልም አል​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ር​ለ​ት​ማ​ለሁ።

7 አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝ፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።

8 ልቤ አን​ተን አለ፦ ፊት​ህን ፈለ​ግሁ፥ አቤቱ፥ ፊት​ህን እሻ​ለሁ።

9 ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ተቈ​ጥ​ተህ ከባ​ሪ​ያህ ፈቀቅ አት​በል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አት​ጣ​ለ​ኝም፥ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ቸል አት​በ​ለኝ።

10 አባ​ቴና እናቴ ጥለ​ው​ኛ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ተቀ​በ​ለኝ።

11 አቤቱ መን​ገ​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ፥ ስለ ጠላ​ቶ​ቼም በቀና መን​ገድ ምራኝ።

12 ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ፈቃድ አት​ስ​ጠኝ፥ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሐሰ​ትም የዐ​መፅ ራስ ነው።

13 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት በሕ​ያ​ዋን ምድር አይ ዘንድ አም​ና​ለሁ።

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ አድ​ርግ፤ በርታ፥ ልብ​ህ​ንም አጽና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተስፋ አድ​ርግ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች