የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 14:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 14:47
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው።


ታና​ሺ​ቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም የወ​ገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም እስከ ዛሬ የአ​ሞ​ና​ው​ያን አባት ነው።


ኤዶም የተ​ባ​ለው የዔ​ሳው ትው​ልድ እን​ዲህ ነው።


የዔ​ሳው ልጆ​ችና መስ​ፍ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የኤ​ዶም ልጆች ናቸው።


ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።


ከሞ​ቱት ደምና ከኀ​ያ​ላን ስብ፥ የዮ​ና​ታን ቀስት ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ የሳ​ኦ​ልም ሰይፍ ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።


የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊ​ትም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


ዳዊ​ትም ደግሞ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ግዛት ለማ​ስ​ፋ​ፋት በሄደ ጊዜ የሱ​ባን ንጉሥ የረ​አ​ብን ልጅ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከጌ​ታው ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር የኰ​በ​ለ​ለ​ውን የኤ​ል​ያ​ዳን ልጅ ሬዞ​ንን ጠላት አድ​ርጎ አስ​ነ​ሣ​በት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስስ ዘንድ አል​ተ​ና​ገ​ረም፤ ነገር ግን በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እጅ አዳ​ና​ቸው።


አሁ​ንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳል፤ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም አር​ፋ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ልጆቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊ​ታ​ችሁ ሄድሁ።


ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ከነ​ገሠ ሁለት ዓመት ሆነው፥


ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከመ​ከ​ተል ተመ​ለሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ስፍ​ራ​ቸው ሄዱ።


በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።


በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች አንድ ሰው በኔ​ሴራ አቅ​ራ​ቢያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ነበረ።