Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ከባድ ጦርነት ነበረ፤ ስለዚህ ሳኦል ብርቱ ወይም ጀግና ሰው ባየ ቍጥር ወደ ራሱ ወስዶ እንዲያገለግለው ያደርግ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ከባድ ጦርነት ነበረ፤ ሳኦልም ብርቱ ወይም ጀግና ሰው ባየ ቍጥር ወደ ራሱ ይሰበስብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 በሳኦልም ዕድሜ ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፥ ሳኦልም ጽኑ ወይም ኃያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰበስብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:52
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።


ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳሙ​ኤል በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልጆ​ቹን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች