መጽሐፈ ጦቢት 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽድቅ የዘመናትን አምላክ ይባርካሉ። በእነዚህ ቀኖች የዳኑ እስራኤላውያን ከልባቸው እግዚአብሔርን ያስታውሱታል። ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ ይሰበሰባሉም፥ ከዛ በኋላም የእነሱ በምትሆን በአብርሃም ምድር ላይ ያለ ሥጋት ይኖራሉ። ከልባቸው እግዚአብሔርን የሚወዱ ደስ ይላቸዋል፤ ኃጢአትንና ክፋትን የሚያደርጉ ግን ከምድር ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል። ሕዝቡም በእርሱ ያምናሉ፤ እግዚአብሔርም ወገኖቹን ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። በእውነትና በቅንነት እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ሁሉ ደስ ይላቸዋል፤ ለወንድሞቻቸውም ቸርነትን ያደርጋሉ። |