ጸሎት ከጾም ጋር፥ ምጽዋትም ከጽድቅ ጋር፥ በተንኰል ከመበልፀግ የበለጡ ናቸው። ወርቅን ከመሰብሰብ ምጽዋት መስጠት ይበልጣል።
ጸሎት ከጾም፥ ከምጽዋትና ከጽድቅ ጋር መልካም ነው። ከብዙ የዓመፅ ገንዘብ ጥቂት የእውነት ገንዘብ ይሻላል፤ ወርቅንም ከማድለብ ምጽዋት መስጠት ይሻላል።