መዝሙር 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ብንያማዊ ሰው ስለ ኩዝ ቃል ለጌታ የዘመረው የዳዊት መዝሙር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! የምተማመንብህ መማጸኛዬ አንተ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ ታደገኝ፤ አድነኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አትጣለኝም፤ ከሚከብቡኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥ |
ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስታውሰኝ ጐብኘኝም፥ የሚያሳድዱኝንም ተበቀልልኝ፤ ቁጣህንም ከማዘግየትህ የተነሣ እንዳታጠፋኝ፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።
ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ።
የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ስለሚደርስ፥ በተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ። በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር መንቀጥቀጥ ምክንያት ከሆነው ሽሽት በበለጠ ትሸሻላችሁ። ከዚያም አምላኬ ጌታ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።