Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 30:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ አንተም ፈወስኸኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም ፈወስከኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፥ ፈጥ​ነ​ህም አድ​ነኝ፤ ታድ​ነኝ ዘንድ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒ​ቴና የመ​ጠ​ጊ​ያዬ ቤት ሁነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 30:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤


አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።


ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።


እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።


ድንቅ ሥራህ በጨለማ፥ ጽድቅህም በሚረሳበት ምድር ትታወቃለችን?


አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባርያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ፥


እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፥ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።


መገሠጽስ ጌታ ገሠጸኝ፥ ለሞት ግን አልሰጠኝም።


አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፥ በእኔም ምክንያት ደስ አይበላቸው።


ጠላቴ እልል አይልብኝምና በዚህም በእኔ እንደ ተደሰትክ አወቅሁ።


የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች