መዝሙር 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽድቄ አምላክ ሆይ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፥ በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፥ ማረኝ፥ ጸሎቴንም ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ ታደርጋላችሁ? እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንስ ትሻላችሁ? ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሰዎች፥ እስከ መቼ ክብሬን ታዋርዳላችሁ? እስከ መቼስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? እስከ መቼስ ሐሰትን ትፈልጋላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ? |
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እንዲህም አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በፊቴ እራስህን ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
ለሁሉም አንድ ዓይነት ዕጣ ክፍል መኖሩ ከፀሐይ በታች በሚደረገው ነገር በሙሉ ይህ ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ በክፋት ተሞልታለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ውስጥ ይኖራል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በመካከላቸውም ስላደረግሁት ተአምራት ሁሉ እንኳ እስከ መቼ ድረስ በእኔ አያምኑም?