Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፥ ከንቱነትንም የተከተሉት፥ ከንቱም የሆኑት ምን ስሕተት አግኝተውብኝ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣ ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣ ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነሆ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኔ ርቀው የሄዱት በኔ ላይ ምን ጥፋት አግኝተው ነው? እነርሱም ከንቱ የሆኑትን ጣዖቶች በማምለካቸው ራሳቸውን ከንቱዎች አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከን​ቱ​ነ​ት​ንም የተ​ከ​ተሉ፥ ከን​ቱም የሆኑ ምን ክፋት አግ​ኝ​ተ​ው​ብኝ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 2:5
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።


የሚሠሩአቸው፥ የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።


ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል።


የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይጠቅማቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያስተውሉም ደግሞ አያውቁም፥ ስለዚህ ያፍራሉ።


እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፤


በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው።


ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰድደዋል፤ አድገዋል ፍሬም አፍርተዋል፤ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።


በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።


ትውልድ ሆይ! የጌታን ቃል ተመልከቱ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንኩባትን? ሕዝቤስ ስለምን፦ ‘እኛ ፈርጥጠናል፤ ዳግመኛ ወደ አንተ አንመጣም’ ይላሉ?


የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ።


እነሆ፦ “ጌታ በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርሷ መካከል የለምን?” የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ አገር ተሰማ። “በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድነው?”


የሰው ልጅ ሆይ፥ ወንድሞችህ፥ ዘመዶችህ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ፥ “ከጌታ ራቁ፥ ምድሪቱ ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች” ብለዋል።


ይህም የእስራኤልን ቤት ለመያዝ ነው፤ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ምክንያት በልባቸው ከእኔ ተለይተዋልና፤


ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ ጌታን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣች።


“ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤


እንዲህም አሉ “እናንተ ሰዎች! ይህን ስለምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፤ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእርነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።


ምክንያቱም እግዚአብሔርን እያወቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን አላከበሩትም ወይም አላመሰገኑትም፤ ነገር ግን ምክንያታቸው ዋጋ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ።


አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በምናምንቴዎቻቸውም አስቆጡኝ፥ እኔም በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፥ በማያስተውል ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ።


ሊጠቅሟችሁ ወይም ሊያድኗችሁ የማይችሉ ከንቱ ነገሮችን አትከተሉ፤ ምክንያቱም ከንቱ ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች