በኪሩቤልም ሠረገላ ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ አንዣበበ።
ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤ በዝናብ ዐዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።
ሁለንተናውን በጨለማ ሸፈነ፤ በውሃ የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ከቦታል።
ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም ብዙ ዋጋ ይቀበላል።
እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ሠረገላውን ደመና የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥
በመከራ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፥ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
የጌታ ክብር ከቤቱ መግቢያ ወጥቶ ከኪሩቤል በላይ ቆመ።
የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፥ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ ለብዙ ትውልድ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።
እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።