Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 91:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 መጠለያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መጠጊያ የሚያደርግ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 91:1
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጭንቅ ትጠብቀኛለህ፥ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።


በመከራ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።


ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች፥ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት፥ አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።


እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ


በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደምን በዛች!


የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መሸሸጊያ፥ ከውሽንፍር መጠለያ፥ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።


ጌታ ጠባቂህ ነው፥ ጌታ በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።


ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፥ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፥ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።


የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት። አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።


ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።


ሬስ። ስለ እርሱ፦ በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት እንኖራለን ያልነው በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጉድጓዳቸው ተያዘ።


ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፥ በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦


ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።


በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በጐልማሶች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል አርቄ ብወስዳቸውም፥ በአገሮች መካከል ብበትናቸውም፥ በሄዱባቸው አገሮች በዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።


እርሱም መቅደስ ይሆናል፤ ለሁለቱ የእስራኤል ቤት ግን የሚያደናቅፍ ድንጋይ የሚያሰናክልም ዐለት ይሆንባቸዋል፤ ለኢየሩሳሌም ሕዝብም ወጥመድና አሽክላ ይሆናል።


የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች