አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ! ተነሥተህ አንተና የኃይልህ ታቦት ወደ ማረፍያ ስፍራህ ሂዱ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።
መዝሙር 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስታዬ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም እደሰታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፥ ፈተንኸኝ፥ ዐመፅም አልተገኘብኝም። |
አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ! ተነሥተህ አንተና የኃይልህ ታቦት ወደ ማረፍያ ስፍራህ ሂዱ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።
ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን ጌታ ደስታዬ ባንቺ ነው ብሏታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።
ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤
እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።