ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥ ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
መዝሙር 115:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ጽኑ ፍቅርህና ስለ እውነትህም ክብርን ስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእኛ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣ ለስምህ ክብርን ስጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ስለ እኛ ሳይሆን ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ ታማኝነትህ ስምህን አክብረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተናገርሁት አመንሁ፤ እኔም እጅግ ታመምሁ። |
ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥ ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ የምሠራው ስለ እናንተ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው በመንግሥታት መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው።
ይህንን የሠራሁት ለእናንተ እንዳልሆና በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።