መዝሙር 115 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በተናገርሁት አመንሁ፤ እኔም እጅግ ታመምሁ። 2 እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ። 3 ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እከፍለዋለሁ? 4 የሕይወትን ጽዋ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ። 5 በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ። 6 የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው። 7 አቤቱ፥ እኔ ባሪያህ ነኝ፥ ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ። 8 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ። 9 በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ፥ 10 በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም። ሃሌ ሉያ። |