ሃሌ ሉያ። የጌታ አገልጋዮች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የጌታንም ስም አመስግኑ።
ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።
እግዚአብሔር ይመስገን! እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ!
እስራኤል ከግብፅ፥ የያዕቆብም ወገን ከጠላት ሕዝብ በወጡ ጊዜ፥
ሃሌ ሉያ። ጌታን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
የዕርገት መዝሙር። እነሆ፥ ጌታን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የጌታ ባርያዎች ሁላችሁ።
የሌዊ ቤት ሆይ፥ ጌታን ባርኩት፥ ጌታን የምትፈሩት ሆይ፥ ጌታን ባርኩት።
አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።
ክፉዎቹን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።
እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና፥ በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል።
ድምፅም ከዙፋኑ እንዲህ ሲል ወጣ፦ “ባርያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤”