Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 134:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዕርገት መዝሙር። እነሆ፥ ጌታን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የጌታ ባርያዎች ሁላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እናንተ በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ እግዚአብሔርን ባርኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እናንተ አገልጋዮቹ! በሌሊት በመቅደሱ የምታገለግሉት ሁሉ፥ ኑ እግዚአብሔርን አመስግኑ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ፤ እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 134:1
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዕርገት መዝሙር። በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ ሰማኝም።


ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለ ሌላ ሥራ በየእልፍኛቸው ይቀመጡ ነበር።


ድምፅም ከዙፋኑ እንዲህ ሲል ወጣ፦ “ባርያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤”


ልጆቼ ሆይ! በፊቱ ቆማችሁ እንድታገለግሉት፥ አገልጋዮቹም እንድትሆኑ፥ እንድታጥኑለትም ጌታ መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”


የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወደ ጌታ ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።


እንዳትሞቱም የጌታን ትእዛዝ እየጠበቃችሁ፥ ለሰባት ቀን ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቀመጣላችሁ፤ እኔ እንዲህ ታዝዣለሁና።”


እርሷም እስከ ሰማኒያ አራት ዓመቷ ድረስ መበለት ነበረች፤ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር።


የዕርገት መዝሙር። ዐይኖቼን ወደ ተራሮቹ አነሣሁ፥ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?


የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ ዳዊትን፥ መከራውንም ሁሉ አስታውስ፥


የዳዊት የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ ልቤ አይታበይም፥ ዐይኖቼም ከፍ ከፍ አይሉም፥ ለትልልቅ ነገሮች፥ ከዐቅሜም በላይ ለሆኑት አልጨነቅም።


ማለዳን ከሚጠብቁ የሌሊት ጠባቂዎች ይልቅ፥ ነፍሴ ጌታን ትጠብቃለች፥ ማለዳን ከሚጠብቁ ጠባቂዎች ይልቅ።


የዕርገት መዝሙር። እስራኤል፦ “ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ” ይበል፥


የመዓርግ መዝሙር። ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።


የዕርገት መዝሙር። ጌታ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።


የዕርገት መዝሙር። በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ።


በዚያን ጊዜ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፥ እርሱንም ለማገልገል በጌታ ፊት እንዲቆም፥ በስሙም እንዲባርክ ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።


የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ እንዴት መልካም፥ እንዴት ውብ ነው።


ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፥ ጌታን ባርኩ።


የዕርገት መዝሙር። ጌታ ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፥ ጌታ ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


የዕርገት መዝሙር። በጌታ የታመኑ እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።


የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦


እነርሱና ልጆቻቸውም በጌታ ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።


ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ይቆማሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ውስጥ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል።


የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።


የእግዚአብሔርንም ቤት የሚጠብቁ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና በዚያ ያድሩ ነበር።


እንደ ሕዝቡም እንደ ወንድሞቻችሁ በየአባቶቻችሁ ቤቶች ሆናችሁ በመቅደሱ ቁሙ፤ ለእያንዳንዱ ለተከፋፈሉትም ለአባቶች ቤቶች ሌዋውያን ይኑሯቸው፤


ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያና ዑኖ በአገልግሎቱ ጊዜ በፊት ለፊታቸው ይቆሙ ነበር።


በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፥ ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑሃል።


ሃሌ ሉያ። የጌታ አገልጋዮች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የጌታንም ስም አመስግኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች