Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 113 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ። የጌታ አገልጋዮች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የጌታንም ስም አመስግኑ።

2 ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የጌታ ስም ቡሩክ ይሁን።

3 ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የጌታ ስም ይመስገን።

4 ጌታ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።

5 እንደ ጌታ እንደ እግዚአብሔር የሚሆን ማን ነው? በላይ የሚኖር፥

6 በሰማይና በምድር ያሉትን ለማየት ዝቅ የሚል፥

7-8 ከመኰንኖች ጋር ከሕዝቡም መኰንኖች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፥

9 መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች