መዝሙር 107:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባቸው በድካም ተዋረደ፥ ተሰናከሉ የሚረዳቸውም አጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በጕልበት ሥራ ልባቸውን አዛለ፤ ተዝለፈለፉ፤ የሚደግፋቸውም አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከባድ ሥራ እንዲጨነቁ አደረጋቸው፤ የሚረዳቸውም ባለማግኘታቸው ተሰናክለው ወደቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራችን ረድኤትን ስጠን፤ በሰውም መታመን ከንቱ ነው። |
ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ንጉሡ ድንገት ከተፍ ብሎ “ይህን መከራ በእኛ ላይ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ እርሱ አንድ ነገር ያደርግ ዘንድ ከዚህ በላይ ምን ልጠብቅ?” አለ።
ስለ ኃጢአታችንም ለሾምህብን ነገሥታት በረከትዋን ታበዛለች፥ ሰውነታችንንም ይገዛሉ፥ በእንስሶቻችንም የሚወድዱትን ያደርጋሉ፥ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን።”
ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
ነፍስሽንም፦ “በአንቺ ላይ እንድንረማመድ ዝቅ በዪ” በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤ ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።
ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል ጌታ፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል ጌታ፥ ስሜም ያለማቋረጥ በየእለቱ ቀኑን ሙሉ ይሰደባል።
ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤
“ከፍልስጥኤማውያን ጋር አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኃይሉ ሲገፋው፥ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው፤ ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ።