ኢሳይያስ 63:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቁጣዬም አጸናኝ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ተመለከትሁ፤ የሚረዳ ግን አልነበረም፤ የሚያግዝ ባለመኖሩም ተገረምሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ ድነትን አመጣልኝ፤ የገዛ ቍጣዬም አጸናኝ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ዙሪያዬን በተመለከትኩ ጊዜ የሚረዳ ማንም አልነበረም። ደጋፊ ባለመኖሩ ተደነቅሁ፤ ስለዚህ በኀይለኛ ቊጣዬ አማካይነት እኔው ራሴ ድልን አመጣሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የሚረዳም እንደሌለ አየሁ፤ የሚያግዝም እንደሌለ ዐወቅሁ፤ ስለዚህ በገዛ ክንዴ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም ወደቀችባቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፥ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፥ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ። ምዕራፉን ተመልከት |