መሳፍንት 16:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 “ከፍልስጥኤማውያን ጋር አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኃይሉ ሲገፋው፥ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው፤ ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 “ከፍልስጥኤማውያን ጋራ አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኀይሉ ሲገፋው፣ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው። ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 “ሕይወቴ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ትለፍ!” ብሎ ጮኸ፤ በሙሉ ኀይሉም በገፋቸው ጊዜ ሕንጻው በፍልስጥኤም ገዢዎቹና እዚያ ባሉት ሁሉ ላይ ተደረመሰ፤ ሶምሶንም በሕይወቱ ሳለ ከገደላቸው ይልቅ በሞተበት ጊዜ የገደላቸው በዙ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ሶምሶንም፥ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶዎቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋቸው፤ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመሳፍንቱ፥ በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወቱ ሳለ ከገደላቸው በዙ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ሶምሶንም፦ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት አለ፥ ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኃይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፥ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ። ምዕራፉን ተመልከት |