የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 104:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነፋሳትን መልእክተኞቹ የሚያደርግ፥ የእሳት ነበልባልም አገልጋዮቹ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መላእክትህን መንፈስ፣ አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነፋስ መልእክተኛህ ነው፤ የእሳት ነበልባልም አገልጋይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ልብ ደስ ይበ​ለው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ትጸ​ና​ላ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊዜ ፊቱን ፈልጉ።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 104:4
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።


ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕ አገልጋይ ዐይኖቹ እንዲከፈቱለት ስላደረገ፥ በኰረብታው ጐን ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተሰልፈው የሚጠብቁት መሆናቸውን ተመለከተ።


እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥


የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።


መልአኩም መልሶ፦ “በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ እነዚህ አራቱ የሰማይ ነፋሳት ናቸው።


ሰዱቃውያን “ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም፤” የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ።


ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ መዳንን ስለሚቀበሉ ሰዎች፥ ለአገልግሎት የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?


ስለ መላእክትም “መላእክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ” ይላል፤